News & Events

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት 6ኛ ዙር፤ 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፤ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የአብክመ ኦዲተር መስሪያ ቤቱን የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት አዳመጠ፤
ለምክር ቤት አባላቱ የክዋኔ ኦዲት ሪፖርቱን ያቀረቡት የክልሉ ዋና ኦዲተር (ዶ.ር) አማረ ብርሃኑ ሲሆኑ በ2014 በጀት ዓመት የተሰሩትን ሁለት የልዩ ኦዲት፣ ስድስት መደበኛ እና አራት የክትትል ኦዲት በድምሩ የ12 ተቋማትን ሪፖርቶች በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ኦዲት ከተደረጉትና ሪፖርታቸው ከቀረበው ተቋማት መካከል የደብረ ታቦር ከተማ ቤቶች እና ኮንስትርክሽን፣ የአማራ ክልል ገጠር መንገድ ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ፣ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ፣ የፍኖተሰላም እና የእንጅባሬ ከተማ አስተዳደሮች፣ መሬት ቢሮ እና የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ የሚሉት ይገኙበታል፡፡
ዋና ኦዲተሩ ሪፖርቱን ሲያቀርቡ እንደገለጹት ኦዲት በተደረጉት ተቋማት የሕዝብ እና የሀገር ሀብት ምዝበራ መፈፀሙን ያሚያሳዩ ግኝቶች መመላከታቸውንና የአሠራር ክፍተቶች መታየታቸውንም ለምክር ቤቱ አብራርተዋል።
ሪፖርቱን ያዳመጡት የምክር ቤቱ አባላትም ኦዲት ማድረግ ብቻ እንደግብ መታየት እንደሌለበት ገልጸው፣ በግኝቶች ላይ ተመሥርቶ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤቱ ግፊት እንዲያደርግ እንዲሁም የክዋኔ እና ክትትል ኦዲት ሥራው ከዚህ በበለጠ ተደራሽ እንዲሆን ጠይቀዋል።
የፍትሕ ተቋማት ከዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ጋር በመቀናጀት የተመዘበረ የሀገር ሀብት እንዲመለስ በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባም የምክር ቤት አባላቱ አሳስበዋል።

 

 

           
Head Office OAG On Google Map Dessie Branch Office
    Email: anrsoag@ethionet.et

    anrsoag11@gmail.com

    Tel +251-58-222-0275

    Tel +251-58-220-0634

    Fax +251-58-220-1694

    P.O.Box 479

    Bahir Dar City, Tana Subcity FelegeHiwot Hospital area

    Email: anrsoag@ethionet.et

    anrsoag11@gmail.com

    Tel   +251-333-117356

        +251-333-117357

    Fax   +251-333

    P.O.Box 479

    Dessie Twon, Bunbua Wuha Subcity