የአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ስልጣንና ተግባር


1. መስሪያ ቤቱ በህግ የተሰጠውን ተግባር ለማከናወን የሚያስፈልገው ሁሉ ይኖረዋል፡፡
በዚህ አጠቃላይ አነጋገር ሳይወሰን መስሪሪያ ቤቱ
2. በዚህ አጠቃላይ አነጋገር ሳይወሰን መስሪያ ቤቱ፡-


ሀ. የክልሉ መንግስት መስሪያ ቤቶች እና ድርጅቶች ሂሳብ ኦዲት ያደርጋል ያስደርጋል፣


ለ. ለክልሉ መንግስት መስሪያ ቤቶችና ድርጅቶች የተለገሱ እርዳታዎችንና ስጦታዎችን ኦዲት ያደርጋል ያስደርጋል፣


ሐ. የክልሉ መንግስት መስሪያ ቤቶችና ድርጅቶች ያስገኙት ውጤት ህጉን የተከተለ፣ ኢኮኖሚያዊ በሆነ አሰራር የተፈፀመ መሆኑንና ተፈላጊው ግብ መምታቱን ለማረጋገጥ የክዋኔ የአካባቢ ጥበቃ ኦዲት ያደርጋል የስደርጋል፤


መ. በክልሉ ውስጥ የመረጃ ኦዲት ያደረጋል፣ ያስደርጋል፤


ሠ. የክልሉ መንግስት መ/ቤቶችና ድርጅቶች አጠቃላይ የቁጥጥር ስርአት በበቂ ሁኔታ መነደፉን፣ በትክክለኛ መንገድና በብቃት ተግባራዊ መሆኑን ለማረጋገጥ የሃብት ቁጥጥር ኦዲት ያደርጋል፣ ያስደርጋል፤


ረ. በመደበኛ ኦዲት ወቅት የአሰራር ግድፈት ወይም ጉድለት ከመገኘቱ የተነሳ አንድ ሂሳብ በልዩ ሁኔታ ኦዲት እንዲደረግ በምክር ቤቱ፣ በክልሉ ፍርድ ቤቶችና በሌሎች የመንግስት መ/ቤቶችና ድርጅቶች አማካኝነት የተጠየቀ እንደሆነ በጉዳዩ ክብደት ላይ ተመስርቶ የእቅዱ አካል በማድረግ ልዩ ኦዲት ያደርጋል፡፡


ሰ. ከዚህ በላይ በሰፈሩ ድንጋጌዎች መሰረት ያከናወነውን የኦዲት ስራ ውጤት ሪፖርት አግባብ ላለው የመንግስት መ/ቤት ወይም ለድርጅቱ ጉድለቱ መከሰቱንና ወንጀል መፈጸሙን የሚያሳይ ሆኖ ቢኖር ለክልል ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት ይገለጻል፡፡  በተጨማሪ ጉዳዩ ከሙስና ጋር የሚያዝ ሆኖ ከተገኘ ለክልሉ ስነ ምግባርና ፀረ- ሙና ኮሚሽን ያሳውቃል፡፡


ሸ. ጉዳዩ ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች እና ድርጅቶች እንዲሁም ከፌዴራልና ከሌሎች ክልላዊ የኦዲት መ/ቤቶች ጋር በመመካከር የኦዲት ደረጃን/ስታንዳርድ/ እና የአሰራር ስርአት መወሰኛ መመሪያዎችን ያወጣል፤


ቀ. ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶችና ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለውስጥ ኦዲተሮች ተገቢውን ስልጠናና የሙያ ምክር ይሰጣል፤ እንደ አስፈላጊነቱም የውስጥ ኦዲት ሪፖርት እንዲቀርብለት ሊያደርግ ይችላል፤
በ. አንድ ሂሳብ ወንጀል ባለበት ሁኔታና ታማኝነት በጎደለው እኳኃን መያዙን ለማመን ምክንያት ያለው እንደሆነ ይህንን ሂሳብ የሚመለከቱ ጽኁፎች፣ መዘክሮች፣ መዝገቦች ሰነዶችና ከነዚሁ ጋር ግንኙነት ያለው ሌሎች መረጃዎችን በማሸግ በመመርመር ውጤቱን ለሚመለከተው አካል ያሳውቃል፡፡


ተ. የክልሉ መንግስት መ/ቤቶችና ድርጅቶች የገንዘብ ሂሳብ አያያዝና አጠባበቅ አስመልክቶ ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ረቂቅ ስራ ላይ አስፈላጊውን ምክርና አስተያየት ይሰጣል፡፡


ቸ. ከሚመለከታቸው የፌዴራና የክልል መንግስት መስሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር የሂሳብ አያያዝ እና የኦዲት ሙያ ትክለኛውን ፊር ይዞ እንዲዳብር ጥረት ያደርጋል፣


ኃ. በክልሉ ውስጥ በኦዲት ሙያ ለሚሰሩ ኦዲተሮች እና የሂሳብ አያያዝ ስራ ለሚያከናውኑ የኦዲት እና ሂሳብ አዋቂዎች በስራው መስክ ለማሰማራት የሚያስችለውን የሙያ ብቃት የምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ያግዳል፣ ይሰርዛል፣ የሙያ ደረጃውን ጠብቀው ማከናወናቸውን ይከታተላል፤ ስልጠናና ምክር ይሰጣል፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘውም በህግ አግባብ ክስ ይመሰርታል፡፡


ነ. የግል ኦዲተሮችንና የሂሳብ አያያዝ ባለሙያዎችን የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ለመስጠት፣ ለማገድ እና ለመሰረዝ የሚያስችል ወጥነት ያለው መመሪያ ያወጣል፤


ኘ. የምስክር ወረቀቶችን በሚሰጥበትና በሚያድስበት ጊዜ በዚህ አዋጅ መሰረት በሚወጣ መመሪያ የሚወሰነውን የአገልግሎት ዋጋ ያስከፍላል፤

 

Power and Duties of the Office

1. The Office shall have all powers necessary for the performance of the duties entrusted to it law.

2. Without being limited to the generality of this statement, the Office shall:

     a. Audit and cause same to be audited the account of the regional Government Offices and organizations;

     b. Audit and cause to be audited assistance and donations given to the regional government offices and organizations;
 
    c. Carry out or cause to be carried out the examination of performance and environmental protection audit to ensure whether the whole system of control of the regional   Government offices and organizations is adequately device and implemented properly and efficiently;

    d. Carry out or cause to carry out information audit in the region;

   e. Carry out cause to be carry out the examination or resources control audit to ensure whether the whole system of the Regional Government Offices and organizations is adequately devised and implemented properly and efficiently;

    f. Undertake special audit assignment based on the seriousness of the matter when requested by the council, regional Courts, other Government Offices and Organizations as well as by the public at large owing to operational mistakes or irregularity to have been identified in the regular auditing period;

   g. Inform audit findings, performed in accordance with the provisions stipulated hereof, to heads of the pertinent office of organization, report to the Bureau of Justice of office or organization, report to the Bureau of Justice of the Region and the Secretariat of the Head of Government, where the audit findings reveal the occurrence of grave irregularity and the commission of a crime; if related to corruption, it also inform to the Ethics and Anti-corruption Commission of the region;

   h. Issue directives of audit standards and operational procedures in consultation with the concerned offices and organizations as well as federal and other regional audit offices;

   i. Provide the required training and certificate of competence there to for internal auditors in cooperation with the concerned offices and organizations; be able to cause internal audit report to be submitted to it, as may be necessary;

    j. Where it has to believe that any account has been kept in a presence of criminal condition and dishonest manner, impound such books, documents, ledgers, vouchers and other materials related to such account; investigate and report the result there to;

   k. Give the necessary advise on the financial control, maintenance of accounts and property administration draft law, regulations and directives to be prepared by offices and enterprises of the Regional Government;

   l. Make efforts, in cooperation with the pertinent federal and regional offices, that the accounting and auditing promotion be promoted geared in the right direction;

  m. Issue, renew, suspend and cancel certificate of competence which enable those auditors performing audit profession and accountants carry out accounting in the region to involve in the field; follow up whether they perform in compliance with the  standard; render training and consultancy; and where necessary, institute and case in accordance with the law;

  n. Issue a uniform directive that enable to issue, suspend and cancel certificates of competence of private auditors and accountants

  o. Charge fee, which is the determined by a regulation issued pursuant to this proclamation, while issuing and renewing certificate of competence.

 

 

 

 

 

 

 

 

 

           
Head Office OAG On Google Map Dessie Branch Office
    Email: anrsoag@ethionet.et

    anrsoag11@gmail.com

    Tel +251-58-222-0275

    Tel +251-58-220-0634

    Fax +251-58-220-1694

    P.O.Box 479

    Bahir Dar City, Tana Subcity FelegeHiwot Hospital area

    Email: anrsoag@ethionet.et

    anrsoag11@gmail.com

    Tel   +251-333-117356

        +251-333-117357

    Fax   +251-333

    P.O.Box 479

    Dessie Twon, Bunbua Wuha Subcity