የኢፎርሜሽን ኮምኒኬሽን ቴክኖሎጅ ልማትና ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት ዋነኛ ዓላማ የመ/ቤቱን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት ለተደራጁ ዋና ዋና እና ደጋፊ ዳይሬክቶሬቶች የሚጠበቅባቸውን ውጤት ለማምጣት እንዲችሉ  ብቃት ያለው የኢፎርሜሽን ሲስተም አገልግሎት በመዘርጋት ደንበኞችና ባለድርሻ አካላት የሚፈልጉትን አገልግሎቶች ለማሟላት፤ ቀልጣፋ ለማድረግ እና ወቅቱን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት ነው፡፡

የቴክኖሎጅ አጠቃቀም እያደገ በመምጣቱ እና የተለያዩ መ/ቤቶች፣ ድርጅቶች እና ተቋማት በዋነኛነት በኮምፒውተር የታገዘ የመረጃ መለዋወጫ መንገዶችን እየመረጡ በመጡበት ወቅት  መ/ቤቱ ዘመናዊ የመረጃ መለዋወጫ እና ደህንነታቸው የተጠበቁ ዘዴዎችን እንዲጠቀም ማድረግ እንዲሁም የቴክኖሎጅ መገልገያ መሳሪያዎችን በተገቢው ቦታ ለማዋል ግንዛቤ ወስዶ በጥንቃቄ መስራት እንዳለበት  እየተከታተል የአቅም ማጐልበት ስራ ኢኮቴልማ ያሰራል ፡፡

የአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኢኮቴ መገልገያ መሣሪያዎችን እና የመረጃዎችን አጠቃቀም በተጨማሪ ደህንነታቸውን በማረጋገጥ የአገልግሎት ጊዜአቸው እንዲራዘም በማድረግ ዋና ኣዲተር መ/ቤቱን ከአላስፈላጊ ወጭ ማዳን ነው፡፡ የዋና ኣዲተር መ/ቤት የኮምፒውተር ተጠቃሚዎች የተለያዩ የመ/ቤቱን ዘርፈ ብዙ አላማዎችን እና የውስጥ አሰራሮችን ለማሳካት በሚንቀሳቀሱበት ወቅት በኢኮቴ መገልገያ መሳሪያዎች አጠቃቀም ዙሪያ ሊያዩት እና ሊተገብሩት የሚገባ አቅጣጫ ያሳያል፡፡

           
Head Office OAG On Google Map Dessie Branch Office
    Email: anrsoag@ethionet.et

    anrsoag11@gmail.com

    Tel +251-58-222-0275

    Tel +251-58-220-0634

    Fax +251-58-220-1694

    P.O.Box 479

    Bahir Dar City, Tana Subcity FelegeHiwot Hospital area

    Email: anrsoag@ethionet.et

    anrsoag11@gmail.com

    Tel   +251-333-117356

        +251-333-117357

    Fax   +251-333

    P.O.Box 479

    Dessie Twon, Bunbua Wuha Subcity