• DSC_5764.jpg
  • DSC_6476.jpg
  • DSC_6491.jpg
  • DSC_6625.jpg
  • DSC_6668.jpg
  • ph1.jpg
  • ph2.jpg
  • ph3.jpg
  • ph4.jpg
  • ph5.jpg
  • ph6.jpg
  • ph7.jpg

Our mandate, duties, and responsibilities emanate from the Regional Constitution, Article 116, and the OAG’s re-establishment Proclamation No. 186/2003 (267/2011 and 287/2015 as amended). These mandates empower us to produce reliable and high-quality reports. The OAG fulfills these mandates by conducting audits in accordance with professional accounting and auditing standards. Through our work, we promote good governance, transparency, and effective accountability in the management and use of public resources. Our mission is pivotal in transforming the lives of citizens by ensuring public funds are used efficiently and effectively.

The primary purpose of this site is to provide convenient access to our reports and to enhance awareness of the role of the Auditor-General. Our reports are public documents, and we encourage you to explore them to understand our work better. By doing so, you can join us in promoting good governance and accountability for the benefit of all.

We hope you find our website resourceful and informative. We welcome your suggestions for further improvements. Your feedback is invaluable as we strive to continuously enhance our services and transparency. Thank you for visiting.

Amare Berhanu Altaseb (PhD)

Auditor General

 
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት 6ኛ ዙር፤ 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፤ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የአብክመ ኦዲተር መስሪያ ቤቱን የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት አዳመጠ፤
ለምክር ቤት አባላቱ የክዋኔ ኦዲት ሪፖርቱን ያቀረቡት የክልሉ ዋና ኦዲተር (ዶ.ር) አማረ ብርሃኑ ሲሆኑ በ2014 በጀት ዓመት የተሰሩትን ሁለት የልዩ ኦዲት፣ ስድስት መደበኛ እና አራት የክትትል ኦዲት በድምሩ የ12 ተቋማትን ሪፖርቶች በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ኦዲት ከተደረጉትና ሪፖርታቸው ከቀረበው ተቋማት መካከል የደብረ ታቦር ከተማ ቤቶች እና ኮንስትርክሽን፣ የአማራ ክልል ገጠር መንገድ ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ፣ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ፣ የፍኖተሰላም እና የእንጅባሬ ከተማ አስተዳደሮች፣ መሬት ቢሮ እና የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ የሚሉት ይገኙበታል፡፡
ዋና ኦዲተሩ ሪፖርቱን ሲያቀርቡ እንደገለጹት ኦዲት በተደረጉት ተቋማት የሕዝብ እና የሀገር ሀብት ምዝበራ መፈፀሙን ያሚያሳዩ ግኝቶች መመላከታቸውንና የአሠራር ክፍተቶች መታየታቸውንም ለምክር ቤቱ አብራርተዋል።
ሪፖርቱን ያዳመጡት የምክር ቤቱ አባላትም ኦዲት ማድረግ ብቻ እንደግብ መታየት እንደሌለበት ገልጸው፣ በግኝቶች ላይ ተመሥርቶ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤቱ ግፊት እንዲያደርግ እንዲሁም የክዋኔ እና ክትትል ኦዲት ሥራው ከዚህ በበለጠ ተደራሽ እንዲሆን ጠይቀዋል።
የፍትሕ ተቋማት ከዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ጋር በመቀናጀት የተመዘበረ የሀገር ሀብት እንዲመለስ በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባም የምክር ቤት አባላቱ አሳስበዋል።
የኦዲት ግኝቶችን ርምጃ አወሳሰድ እና ማሻሻያ ትግበራን ለማጠናከር ድጋፍ እና ክትትል ማድረግ ይገባል።

ባሕር ዳር: የካቲት 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 9ኛ መደበኛ ጉባኤ የሦስተኛ ቀን ጉባኤውን እያካሄደ ነው። ምክር ቤቱ በሦስተኛ ቀን ውሎው የአማራ ክልል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት አዳምጧል።

የአማራ ክልል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትን ዋና ኦዲተር አማረ ብርሃኑ (ዶ.ር)
አቅርበዋል።

በክልሉ በኦዲት ተደራጊ ተቋማት ላይ የኦዲት ሥራ እየሠሩ መኾናቸውን ገልጸዋል። ስጋተ ኦዲት ያለባቸውን መሥሪያ ቤቶች የቅድሚያ ቅድሚያ በመስጠት የፋይናንስ እና ሕጋዊነት የኦዲት ሽፋን እንዲያገኙ እንደሚያደርጉም አንስተዋል።

የክልሉን የልማት የትኩረት አቅጣጫዎች፣ ትልልቅ ፕሮጀክቶች፣ የሕዝብ ጥያቄ ያለባቸው ተቋማትን በመለየት የተቋማትን ውጤታማነት በክዋኔ ኦዲት እያረጋገጠ መኾኑን ገልጸዋል። የተቋሙን ነጻነት እና ገለልተኛነት ለማጠናከር እየሠሩ መኾናቸውን አንስተዋል።

በተለያዩ ተቋማት ላይ የኦዲት ሥራ መሥራታቸውንም ገልጸዋል። የፋይናንስ አሥተዳደር ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት በትክክል ሥራ ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ በተከናወነ የኦዲት ሥራ የሂሳብ አያያዝ ግድፈቶች፣ የውስጥ ቁጥጥር ድክመቶች እና የሕግ ጥሰት የታየባቸው መኖራቸውን ተናግረዋል።

የማጭበርበር ድርጊት የሚፈጥሩ አሠራሮችን እየፈተሹ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት ማምከን እና የአጥፊዎችን ተጠያቂነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል። የመንግሥት ፕሮጀክቶች አፈጻጸም እንዲሻሻል ቅንጅታዊ አሠራሮችን እና የመረጃ ልውውጥን ማጠናከር ይገባል ነው ያሉት።

የኦዲት ግኝቶችን ርምጃ አወሳሰድ እና ማሻሻያ አስተያየቶች ትግበራን ለማጠናከር ድጋፍ እና ክትትልን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባዋል ብለዋል። በክልሉ ኦዲት ተደራጊ ቁጥር መብዛት እና በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የልዩ ኦዲት ፍላጎት ተደራሽ ለማድረግ ለረጅም ጊዜ ሳይሻሻል የቆነው የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት መዋቅራዊ አደረጃጀት ትኩረት ሊያገኝ ይገባል ነው ያሉት።

የምክር ቤት አባላት በጀትን በአግባቡ ለመጠቀም ቁጥጥር እና ክትትል ማድረግ ይገባል ብለዋል። የኦዲት የማስመለስን አቅም ማሳደግ እና ሃብትን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ አንስተዋል።

ለጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት የአማራ ክልል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ዋና ኦዲተሩ በተሠሩት ሥራዎች ኦዲት የማስመለስ አቅም እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። ውጤታማ ሥራ ለመሥራት የውስጥ ኦዲተርን ማጠናከር ይገባል ነው ያሉት።

በክልሉ የተፈጠረው የጸጥታ ችግር በሁሉም አካባቢዎች ላይ በተሟላ መንገድ ሥራ መሥራት አለመቻላቸውንም ተናግረዋል።
 
 
 
 

 

 

 

 

 

 

 


 

           
Head Office OAG On Google Map Dessie Branch Office
    Email: anrsoag@ethionet.et

    anrsoag11@gmail.com

    Tel +251-58-222-0275

    Tel +251-58-220-0634

    Fax +251-58-220-1694

    P.O.Box 479

    Bahir Dar City, Tana Subcity FelegeHiwot Hospital area

    Email: anrsoag@ethionet.et

    anrsoag11@gmail.com

    Tel   +251-333-117356

        +251-333-117357

    Fax   +251-333

    P.O.Box 479

    Dessie Twon, Bunbua Wuha Subcity