Mandate

አብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ስልጣንና ተግባር

መስሪያ ቤቱ በሕግ የተሰጠውን ተግባር ለማከናወን የሚያስፈልገው ሥልጣን ሁሉ የሚኖረው ሆኖ በዚህ አጠቃላይ አነጋገር ሳይወሰን በሦስቱ የመቋቋሚያ ፣ መወሰኛና ማሻሻያ አዋጆች መሰረት፡- 

  1. አዋጅ ቁጥር 186/2003

  2. የክልሉ መንግስት መስሪያ ቤቶች እና ድርጅቶች ሂሳብን ኦዲት ያደርጋል ፣ ያስደርጋል፤
  3. ለክልሉ መንግስት መስሪያ ቤቶችና ድርጅቶች የተለገሱ እርዳታዎችንና ስጦታዎችን ኦዲት ያደርጋል፤ ያስደርጋል፤
  4. የክልሉ መንግስት መስሪያ ቤቶችና ድርጅቶች ያስገኙት ውጤት ሕጉን የተከተለ፣ ኢኮኖሚያዊ በሆነ አሰራር የተፈጸመ መሆኑንና ተፈላጊውን ግብ መምታቱን ለማረጋገጥ የክዋኔና የአካባቢ ጥበቃ ኦዲት ያደርጋል፤ ያስደርጋል፤
  5. በክልሉ ውስጥ የመረጃ ኦዲት ያደርጋል፤ ያስደርጋል፣
  6. የክልሉ መንግስት መ/ቤቶችና ድርጅቶች አጠቃላይ የቁጥጥር ስርዓት በበቂ ሁኔታ መነደፉን ፣በትክክለኛ መንገድና በብቃት ተግባራዊ መሆኑን ለማረጋገጥ የሀብት ቁጥጥር ኦዲት ያደርጋል፤ ያስደርጋል፤
  7. በመደበኛው ኦዲት ወቅት የአሰራር ግድፈት ወይም ጉድለት ከመገኘቱ የተነሳ አንድ ሂሳብ በልዩ ሁኔታ ኦዲት እንዲደረግ በምክር ቤቱ ፤ በክልሉ ፍርድ ቤቶችና በሌሎች የመንግስት መ/ቤቶችና ድርጅቶች አማካኘነት የተጠየቀ እንደሆነ በጉዳዩ ክብደት ተመስርቶ የዕቅዱ አካል በማድረግ ልዩ ኦዲት ያደርጋል፡፡
  8. ከዚህ በላይ በሰፈሩ ድንጋጌዎች መሰረት ያከናወነውን የኦዲት ስራ ውጤት ሪፖርት አግባብ ላለው የመንግስት መስሪያ ቤት ወይም ለድርጅት የበላይ ኃላፊ ያሳውቃል፡፡ የኦዲት ውጤቱ ከፍተኛ ጉድለት መከሰቱንና ወንጀል መፈጸሙን የሚያሳይ ሆኖ ሲገኝ ይህንኑ በግልባጭ ለክልሉ ፍትህ ቢሮና ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ይገልጻል፡፡ ጉዳዩ ከሙስና ጋር የሚያያዝ ሆኖ ከተገኘም ለክልሉ የጸረ- ሙስና መርማሪ አካለት ያሳውቃል፡፡
  9. ጉዳዩ ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች እና ድርጅቶች እንዲሁም ከፌዴራልና ከሌሎች ክልላዊ የኦዲት መ/ቤቶች ጋር በመመካከር የኦዲት ደረጃን /ስታንዳርድ/ እና የአሰራር ስርዓት መወሰኛ መመሪያዎችን ያወጣል፤
  10. ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶችና ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለውስጥ ኦዲተሮች ተገቢውን ስልጠናና የሙያ ምክር ይሰጣል፤ እንደአስፈላጊነቱም የውስጥ ኦዲት ሪፖርት እንዲቀርብለት ሊያደርግ ይችላል፣
  11. አንድ ሂሳብ ወንጀል ባለበት ሁኔታና ታማኘነት በጎደለው አኳኋን መያዙን ለማመን ምክንያት ያለው እንደሆነ ይህንን ሂሳብ የሚመለከቱ ጽሁፎች ፣ መዘክሮች ፣ መዝገቦች ፣ ሰነዶችና ከነዚሁ ጋር ግንኙነት ባላቸው ሌሎች መረጃወች ላይ በማሸግና በመመርመር ውጤቱን ለሚመለከተው ያሳውቃል፡፡
  12. የክልሉ መንግስት መ/ቤቶችና ድርጅቶች የገንዘብና ንብረት ሂሳብ አያያዝና አጠባበቅ አስመልክቶ በሚያዘጋጁዋቸው ማንኛውም ህጎች፤ ደንቦችና መመሪያዎች ረቂቅ ስራ ላይ አስፈላጊውን ምክርና አስተያየት ይሰጣል፡፡
  13. ከሚመለከታቸው የፌዴራልና የክልል መንግስት መስሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር የሂሳብ አያያዝ እና የኦዲት ሙያ ትክክለኛውን ፈር ይዞ እንዲዳብር ጥረት ያደርጋል፤)
  1. አዋጅ ቁጥር 267/2011፤

  1. አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የፋይናንስና ህጋዊነት ኦዲት ሥራን የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ላላቸው የግል ኦዲተሮች ኦዲት እንዲያደርጉ በመስጠት የኦዲት ደረጃውን ጠብቆ ስለመከናወኑ ይቆጣጠራል ያረጋግጣል፡፡
  2. የኦዲት ተግባሩን እንዲከናውኑ ሃላፊነቱ የተሰጣቸው የግል ኦዲተሮች በተመለከተ የመመልመያ መስፈርቶች ተያያዥ ጉዳዮች የሚወስን ዝርዝር የአፈጻፀም መመሪያ ያወጣል፡፡
  3. የክልሉ መንግስት የልማት ድርጅቶችና የህዝብና የመንግስት ጥቅም ያለባቸው አካላትን አስመልክቶ ኦዲት እንዲደረጉ በፍትህ አካላትና በሌሎችም ጉዳዩ በሚመለከታቸው ተቀቋማት የሚቀርቡ ትዕዛዝና ጥያቄዎችን በመቀበል ኦዲት ሊያደርግ / ሊያስደርግ ይችላል፡፡
  4. ከላይ በተራ ቁጥር 14 እና 15 የተገለጹትን ተግባራት ለማስፈጸም ይቻል ዘንድ የክልሉ መንግስት እንደአስፈላጊነቱ በራሱ ገቢ የሚተዳደርና በሙያው ለክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ተጠሪ የሆነ ክልላዊ የኦዲት ሰርቪስ ኮርፖሬሽን ሊያቋቁም ይችላል፡፡ ዝርዝር አደረጃጀቱ በደንብ ይወሰናል፡ 

3.  አዋጅ ቁጥር 287/2015

17.  የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና        ኦዲተር መ/ቤት በክልሉ ውስጥ          ለሚኖሩና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ እና የድርጅት የምስክር ወረቀት ለማግኘት መስፈርቱን አሟልተው ለሚያመለክቱ ባለሙያዎች በኦዲት ሙያ ወይም በሒሳብ አያያዝ ሥራ መሠማራት የሚያስችላቸውን የሙያ ብቃት ማረጋጋጫ እና የድርጅት የምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ ይከታታላል፣ ያድሳል፣ ያግዳል፣ ይሠርዛል፣ ስልጠናና ምክር ይሰጣል፣ ጥፋት ተፈጽሞ ሲገኝ የዲስፕሊን ክስ ይመሠርታል፣ ወይም በሕግ አግባብ እንዲጠየቁ ለሚመለከተው የፍትሕ አካል ጉዳዩን ያስተላልፋል፡፡

18. በየደረጃው ባሉ የፍትህ አካላት በሕግ የተያዙ የኦዲት ግኝቶች ያሉበት ደረጃ በአብክመ ፍትሕ ቢሮ እንዲሁም በፖሊስ ኮሚሽን ተጠቃለው የአፈፃፀም ሪፖርት ለዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በየሦስት ወሩ እንዲደርሰው ይደረጋል፤ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤትም አተገባበሩን እና ከተጠቀሱት አካላት ያገኘውን የግኝት አመላለስ ማስረጃ አካቶ ለክልሉ ምክር ቤት ሪፖርት ያቀርባል የሚሉት ለመ/ቤቱ ከተሰጡት ስልጣንና ተግባር ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

Powers And Duties Of The Office of auditor general

The Office Shall Have All Powers Necessary For The Performance Of The Duties Entrusted To It By Law. With Out Being Limited To The Generality Of This Statement, The Office Shall:-

Proclamation 186/2011

  1. Audit And Cause Same To Be Audited The Account Of The Regional Government Offices And Organizations;
  2. Audit And Cause To Be Audited Assistances And Donations Given To The Regional Government Offices And Organizations;
  3. Carry Out Or Cause To Be Carried Out The Examination Of Performance And Environmental Protection Audit To Ensure Whether The Whole System Of Control Of The Regional Government Offices And Organizations Is Adequately Devised And Implemented Properly And Efficiently;
  4. Carry Out Or Cause To Carry Out Information Audit In The Region;
  5. Carry Out And Cause To Be Carry Out The Examination Of Resources Control Audit To Ensure Whether The Whole System Of The Regional Government Offices And Organizations Is Adequately Devised And Implemented Properly And Efficiently;
  6. Undertake Special Audit Assignment Based On The Seriousness Of The Matter When Requested By The Council, Regional Courts, Other Government Offices And Organizations As Well As By The Public At Large Owing To Operational Mistakes Or Irregularities To Have Been Identified In The Regular Auditing Period;
  7. Inform Audit Findings , Performed In Accordance With The Provisions Stipulated Hereof, To Heads Of The Pertinent Office Or Organization , Report To The Bureau Of Justice Of The Region And The Secretariat Of The Head Of Government, Where The Audit Findings Reveal The Occurrence Of Grave Irregularity And The Commission Of A Crime; If Related To Corruption , It Also Inform To The Ethics And Anti- Corruption Commission Of The Region;
  8. Issue Directives Of Audit Standards And Operational Procedures In Consultation With The Concerned Offices And Organizations As Well As Federal And Other Regional Audit Offices
  9. Provide The Required Training And Certificate Of Competence There To For Internal Auditors In Cooperation With The Concerned Offices And Organizations; Be Able To Cause Internal Audit Report To Be Submitted To It, As May Be Necessary;
  10. Where It Has To Believe That Any Account Has Been Kept In A Presence Of Criminal Condition And Dishonest Manner, Impound  Such Books, Documents, Ledgers, Vouchers And Other Materials Related To Such Account; Investigate And Report The Result Thereto;
  11. Give The Necessary Advise On The Financial Control, Maintenance Of Accounts And Property Administration Draft Laws, Regulations And Directives To Be Prepared By Offices And Enterprises Of The Regional Government;
  12. Make Efforts, In Cooperation With The Pertinent Federal And Regional Offices , That The Accounting And Auditing Promotion Be Promoted Geared In The Right Direction;

       Proclamation 267/2019

  1. When It Gets Necessary, It Gives The Finance And Legal Audit Work To Private Auditors Who Have Certificate Of Quality Assurance To Audit, And It Controls And Ensures The Work Whether It Is Done Based On Standard.
  2. . Issues Particular Performance Directives Of Recruitment Criteria And Other Related Cases Concerning Private Auditors Who Have Given Responsibility To Carry Out The Audit Work.
  3. It May Audit And Cause To Be Audited Concerning The Regional Public Development Organizations And Bodies Those Have Public And Government Interests When Orders Are Presented By Justice Bodies And Other Concerning Institutions To Make Audit.
  4. So As To Enable To Cause The Execution Of The Activity Stipulated In Sub-Article 2 Of This Article Above, The Regional State May, As Deemed As Necessary, Establish A Regional Audit Service Corporation Which Is Administered In Its Own Revenue And Accountable To The Regional Auditor General In Its Profession. The Detail Structure Shall Be Determined By A Regulation.

Proclamation 287/2023

  1. The Amhara National Regional State Office Of General Auditor Shall Provide Professional Qualification Assurance And Organization Certificate, Which Enables Them To Be Engaged In Auditing And Accounting Profession, To Professionals Who Live In The Region And Request Same Meeting The Requirements To Obtain Professional Qualification Assurance Certificate; Follows Up, Renews, Suspends, Cancels, Provides Training And Counseling, Institutes Disciplinary Sue When An Offence Is Committed, Or Forwards The Case To The Relevant Justice Organ So That They Shall Be Accountable To The Proper Law.
  2. Performance Report Showing The Level Of Audit Finding That Are Bound By Law By Judicial Bodies At All Levels Shall Be Submitted To The Amhara National Regional State Auditor General Office In Every Three Months Summarized By The Amhara National Regional State Justice Bureau As Well As By Police Commission; The General Auditor Office Shall Submit A Report To The Region Council Including The Implementation And Evidence Of Finding From The Mentioned Bodies
Scroll to Top