About OAG

የመስሪያ ቤቱ ታሪካዊ ዳራና የህግ ማዕቀፍ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋና ኦዲተር መ/ቤት በሀምሌ 1985 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 6/1986 የክልል ሦስት የሽግግር መስተዳደር የኦዲት መ/ቤት በሚል የተቋቋመ ሲሆን በዚህ መቋቋሚያ አዋጅ መሠረት የመ/ቤቱ ዋና ኦዲተር እና ም/ዋና ኦዲተር በክልሉ ሊቀመንበር አቅራቢነት በክልሉ ምክርቤት እና የመምሪያ ሃላፊዎች ደግሞ በዋና ኦዲተሩ አቅራቢነት በክልሉ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንደሚሾሙ ይገልጻል፡፡ የዋና ኦዲተሩ ተጠሪነት ለክልሉ ምክር ቤት ሲሆን የበታች የሥራ ኃላፊዎችና ኦዲተሮች ደግሞ ተጠሪነታቸው በየደረጃው የሚገኙ ለበላይ ኦዲተር መ/ቤት ኃላፊዎች ይሆናል፡፡ እንደአስፈላጊነቱ በየዞኑ የሚቋቋሙ ቅርንጫፍ መ/ቤቶች እንደሚኖሩት በዚህ መቋቋሚያ አዋጅ ተገልጿል፡፡

የመ/ቤቱ ማቋቋሚያ አዋጅ ባለፉት 30 ዓመታት ለአምስት ጊዜያት ማሻሽያ የተደረገበት ሲሆን :-

  1. አዋጅ ቁጥር 6/1988 ይህ አዋጅ የክልሉ ህገ-መንግስት መጽደቅን ተከትሎ የወጣ የማሻሽያ አዋጅ ሲሆን ከአዋጅ ቁጥር 6/1986 የሚለየው የመ/ቤቱ መጠሪያ ስያሜ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንገስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት መባሉ እና የመ/ቤቱ ኃላፊዎች አንድ ዋና ኦዲተር እና የመምሪ ሃላፊዎች ሲኖሩት የሹመት አሰጣጡን በተመለከተ የዋና ኦዲተሩ ሹመት በክልሉ ህገ-መንግስት አንቀጽ 99/1 መሠረት የሚፈጸም እንደሆነ እና የመምሪያ ሃላፊዎች ሹመት ደግሞ በዋና ኦዲተሩና በርዕሰ መስተዳደሩ ተመርጠው በርዕሰ መስተዳደሩ አቅራቢነት በክልሉ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንደሚሾሙ ይገልፃል፡፡ እንደአስፈላጊነቱም ቅርንጫፍ መ/ቤቶች እንደሚኖሩት በማሻሽያ አዋጁ ተገለጿል፡፡
  2. አዋጅ ቁጥር 98/1996 ይህ የማሻሽያ አዋጅ የዋና ኦዲተር መ/ቤት ከአስፈጻሚው አካል ነጻና ገለልተኛ ሆኖ የኦዲት ሥራውን እንዲያከናውን የወጣ አዋጅ ሲሆን በዚህ የማሻሽያ አዋጅ የተካተቱ አንቀጾች የዋና ኦዲተር መ/ቤቱ ድርጅታዊ መዋቅር በተመለከተ ዋና ኦዲተር፤ ምክትል ዋና ኦዲተር፤ የኦዲት ዳይሬክተሮች፣ የኦዲት ስራ አስኪያጆችና ሌሎች አስፈላጊ ባለሙያዎች ይኖሩታል በሚል የተገለጸ ነው፡፡ የዋና ኦዲተሩና ም/ዋና ኦዲተሩ ሹመት በተመለከተ በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቅራቢነት በምክርቤቱ የሚሾሙ ሲሆን ዋና ኦዲተሩና ም/ዋና ኦዲተሩ ከፖሊቲካ አባልነት ገለልተኛ መሆን እንዳለባቸው እና የሁለቱም የሥራ ዘመን 12 ዓመት እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ከስልጣን የሚነሱባቸው ምክንያቶችም በአዋጁ በዝርዝር የተቀመጡ ናቸው፡፡ የመ/ቤቱ ሒሳብ ምክርቤቱ በሚሰየሙ ብቁና ገለልተኛ በሆኑ ኦዲተሮች ተመርምሮ ውጤቱ ለምክርቤቱ እንደሚቀርብ እና መ/ቤቱና ዋና ኦዲተሩ ተጠሪነታቸው ለምክርቤቱ ሲሆን ምክ/ዋና ኦዲተሩ ተጠሪነት ደግሞ ለዋና ኦዲተሩና ለምክርቤቱ ይሆናል በማለት የማሻሽያ አዋጁ የዋና ኦዲተር መ/ቤቱን ገለልተኛነትና ነጻነት ያረጋገጠ አዋጅ ተብሎ ሊጠራ የሚችል ነው፡፡
  3. አዋጅ ቁጥር 186/2003 ይህ የማሻሽያ አዋጅ ያስፈገበት ምክንያት በወቅቱ የተካሄደው የመሠረታዊ የሥራ ሂደት አሠራር ለውጥ ጥናት (BPR)፣ የBPR ጥናቱን ተከትሎ የተገኙ ለውጦች ሲሆኑ በአጠቃላይ ሲታይ በአዋጅ ቁጥር 98/1996 ያሉ አንቀጾች ላይ መሠረታዊ ለውጥ ሳያደርግ በወቅቱ የነበረውን የ(BPR)ን ጥናት አደረጃጀት ተከትሎ የነበሩ ለውጦችንና ለተቋሙ የተሰጡ ተጨማሪ ስልጣንና ተግባራትን በማካተት የወጣ አዋጅ ነው፡፡
  4. በአዋጅ ቁጥር 267/2011 ይህ የማሻሻያ አዋጅ እንዲወጣ እንደመነሻ የተወሰዱ ጉዳዮች ከመ/ቤቱ አደረጃጀት ለውጥ ጋር በተያያዘ የሠራተኞች የሲቪል ሰርቪስና ኦዲተሮች ደንብ በሚል መከፈሉ እና የኦዲት ሽፋንን ከማሳደግ አኳያ መ/ቤቱ የኦዲት ሥራን በውክልና የማሠራት ሁኔታ የአሠራር መመሪያዎችን ማውጣት የሚችልበት ተጨማሪ ስልጣንና ተግባር መስጠቱ የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡
  5. አዋጅ ቁጥር 287/2015 ይህ የማሻሽያ አዋጁ የወጣበት ዋና ዓላማ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት ጥራትና ሽፋንን ለማሳደግ እና የኦዲት መ/ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን የመረጃ ልውውጥ ለማጠናከር ተጨማሪ አንቀጽ ማካተት አስፈላጊ ሆኖ በመገኙቱ እንደሆነ ይገልፃል፡፡

መ/ቤቱ የመጨረሻዎቹን ሦስቱን የማሻሽያ አዋጆች እኩል በሥራ ላይ እየተጠቀመ ይገኛል፡፡

 Historical background and legal framework of the office

The Office of the Chief Auditor of the Amhara National Regional Government was established in July 1985 by proclamation No. 6/1986 as the Office of the Audit of the Transitional Administration of Region Three. According to this establishment, the Auditor General and the Office of Auditor general are represented by the Chairman of the Region in the Regional Council, the Heads of Departments are represented by the Auditor General and it states that an executive committee will be appointed.

The auditor general is accountable to the regional council, whiles the subordinate officers and Vice G/auditors is accountable to the auditors general at each level. It is stated in this establishment that there will be branch offices established in each zone as needed. In the past 30 years, the office establishment proclamation has been revised five times;

1. Proclamation No.6/1988 This Proclamation is an amendment promulgation issued following the approval of the constitution of the region. The name of the office is different from Proclamation No. 6/1986. And When the officials of the office have one auditor-general and heads of department, regarding the appointment of the auditor-general is done in accordance with Article 99/1 of the state constitution, and the appointment of department heads is to be selected by the auditor-general and the directorate and appointed by the regional executive committee on the recommendation of the auditor general. It is stated in the amendment decree that there will be branch offices as necessary.

2. Proclamation No. 98/1996 this amendment decree is issued to make the Office of the Auditor General independent from the executive body to carry out its audit work. Stated that it will have Deputy Auditor General, audit directors, audit managers and other important professionals regarding the appointment of the Auditor-General and deputy auditor General they are appointed by the council on the recommendation of the head of the region. It is stated that the Auditor General and the Vice Auditor General must be independent from politics and the tenure of both of them is 12 years, it has been announced and the reasons for resignation are detailed in the decree. The amendment decree that the accounts of the office will be examined by qualified and independent auditors appointed by the council and the results will be presented to the council and the office and the auditor general will be accountable to the council and the deputy auditor general will be accountable to the auditor general and the council.

3. 186/2003 the reason for the Amendment Proclamation was the basic work process change study Business process reengineering (BPR) conducted at the time, and the changes found following the BPR study. In general, it is a decree issued by incorporating the changes that followed the organization of the (BPR) study at the time and the additional powers and functions given to the office, without making any fundamental changes to the articles of Decree No. 98/1996.

4. In Proclamation No. 267/2011, the issues taken as a starting point for the issuance of this amendment decree are the payment of employees as civil service and auditors regulations in relation to the change in the organization of the office, and the provision of additional powers and functions in which the office can issue operational guidelines for the delegation of audit work in order to increase audit coverage.

5.  Proclamation No. 287/2015 states that the main purpose of this amendment is to increase the quality and coverage of the audit of the Amhara National Regional Government Auditor General’s Office and to strengthen the information exchange between the Audit Office and stakeholders. The office is using the last three amendments equally in force.

Scroll to Top